ህብረተሰቡ የሚነሳው የመሰረተ ልማት ይሟላልን ጥያቄ የሚፈታው በቂ ገቢ በመሰብሰብ ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ገለፁ ፡፡

 የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ “ግብር፤ ለሀገር ክብር” በሚል መሪ መልዕክት በተካሄደው የንቅናቄ መድረክ በ2015 በጀት ዓመት የታክስ ህግን አክብረው በመስራት የተሻለ ግብር ለከፈሉ ታማኝ ግብር ከፋዮች፣ ለታታሪ ሠራተኞች እና አጋር አካላት የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ፤ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ፤ የኢፊድሪ ገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተካፋይ ሆነዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ  እንደተናገሩት ህዝብና መንግስት ተገናኝተው በሚወያዩበት ጊዜ ከህብረተሰቡ የሚነሳው ጥያቄ የመሰረተ ልማት ይሟላልን ጥያቄ ይገኛበታል፡፡ ይህን ለመመለስ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በተገቢው መልኩ ትኩረት

ርዕሰ መስተዳደሩ በመልዕክታቸው ግብር በመክፈል ዛሬ ምሳሌ የሆናችሁ ግብር ከፋዮች እንደሌሎች ገንዘብ በመሰብሰብ መክበር እንደምትችሉ ብታውቁም ከህዝባችን አንነጥቅም፣ ከድሃው ኪስ የተሰበሰበውን አንውስድም በማለት ግብር ስለከፈላችሁ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል፡፡

ባለፉት አመታት በክልሉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ጠንካራ የግብር አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት እና ገቢውን ለማሳደግ እርብርብ በመደረጉ አዳጊ ገቢ እየተሰበሰበ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለአብነትም በ2015 በጀት ዓመት ቢሮው ለመሰብሰብ ካቀደው 42.85 ቢሊዮን ብር ውስጥ 38.05 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ የተቋሙን ጥረት የሚያሳይ እንደሆነ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረት ማህሙድ ተናግረዋል፡፡

ለ74 ግለሰብ ግብር ከፋዮች፣ ለ7 የልማት ድርጅቶች፣ በ2015 በጀት ዓመት ገቢ አሰባሰብ ላይ በአጋርነት አስተዋጽኦ ለነበራቸው 27 ተቋማት እና በተቋሙ ታታሪ ተብለው ለተመረጡ 45 ሰራተኞች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

en_US