አቶ ሀብታሙ ጌታሁን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ በሰጡት መግለጫ መምሪያው በ2016 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ ብር 2,048,361,897 ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ብር 825,713,869 ወይም የእቅዱን 40.31 በመቶ መሰብሰቡን አሳውቀዋል።

ይህ ገቢ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ብር 738,050,204 ጋር ሲነጻጸር በብር 87,663,665 ወይም 11.88 በመቶ ብልጫ ያለው አለው ብለዋል።

አቶ ሀብታሙ አክለው እንደገለጹት ገቢው ከ15 የወረዳና በ4 የከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤቶች ከተለያዩ የገቢ አርስቶች የተሰበሰበ ነው።

የተሻለ ገቢ ሊሰበሰብ ከቻለበት ዋና ዋና ተጠቃሽ ምክንያቶችን

አንደኛ የግብር ከፋዩ ግብር የመክፈል ባህል በየጊዜው እያደገ የመጣ መሆኑ፣

ሁለተኛ ህገ-ወጥና አዳዲስ ግብር ከፋዮችን ወደ ግብር መረቡ ማስገባት መቻሉ፣

ሦስተኛ መምሪያው ከዚህ በፊት በክልሉ የወረዱ አዳዲስ አሰራሮችንና መመሪያዎችን በወረዳና በከተማ አስ/ገቢ ጽ/ቤት ደረጃ በአግባቡ እንዲተገበሩ ጥብቅ የሆነ የድጋፍና የክትትል ስርዓት በመዘርጋቱ እና

አራተኛ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤት ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ኃላፊነታቸውን በቁርጠኝነትና በታማኝነት መወጣት መቻላቸው ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል በዚህ ዓመት የአጋርና የባለድርሻ አካላት እንዲሁም በየደረጃው ያለው አመራር ተሳትፎም ከምንጊዜው በላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

መምሪያ ኃላፊው በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራቶች ውስጥ በዞኑ ስር የሚገኙ ሁሉም የገቢ ተቋማት የበጀት ዓመቱን የገቢ ዕቅድ ከበጀት ዓመቱ ባጠረ ጊዜ በብቃትና ሙሉ በሙሉ በመሰብሰብ የህ/ሰቡን የመልማት ጥያቄ መመለስ የሚያስችል ያደገ ገቢ ለመሰብሰብ ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአቶ ማስረሻ ባየ === // === የመምሪያው ግብር ትም/ትና ኮሙ/ን ስራ ሂደት አስተባባሪ

am