የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ8 ወራት 1,197,054,955.87 ወይም 39.77 በመቶ ሰበሰበ

አቶ ታረቀኝ ተፈራ – – – // – – – የዞኑ ግብርትምህርትና ኮሚኒኬሽን ስራ ሂደት አስታበባሪ

የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት ከመደበኛ ገቢ ብር 2600248607 እናከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 40,978,210 በድምሩ ብር3,010,030,817 ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም ከመደበኛ ገቢ ብር 1,083,933,521.24 ወይም 41.69 በመቶ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 113,121,434.63 ወይም 27.61 በመቶ በድምሩ ብር 1,197,054,955.87 ወይም 39.77 በመቶ አሳክቷል።

መምሪያው በቀሪ 4 ወራት ቀሪውን 1.8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ባሉትን ጸጋዎች የወረዳና ከተሞችን አፈጻጸም በመለየት የተጠናከረ ድጋፍ በማድረግ ዕቅዱን ማሳካት እንደሚገባ ከማኔጅመንት አባላት ተወስኖ የጋራ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

am